ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በወርቃማ የሰኞ ማለዳ የ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በወርቃማ የሰኞ ማለዳ የአብሮነት መድረክ በከተማ ደረጃ ተሸላሚ ለሆኑ ዳይሬክቶሬቶች እውቅና ሰጠ

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በወርቃማ የሰኞ ማለዳ የአብሮነት መድረክ በከተማ ደረጃ ተሸላሚ ለሆኑ ዳይሬክቶሬቶች እውቅና ሰጠ

                 ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም
                     **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዘወትር ሰኞ ማለዳ አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች የሚሳተፉበት ልምድና ዕውቀት ተሞክሮ የሚጋራበት የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ አካሂድዋል፡፡

በአብሮነት መድረኩ ላይ ከኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ንጋቱ "የተግባቦት ክህሎት" በሚል ርዕስ ሰነድ በማቅረብ የህይወት ፣ የዕውቀትና የስራ ተሞክሮአቸውን በመድረኩ አጋርተዋል

በመድረኩ የባለስልጣኑ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ የአንኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ስለመድረኩ አስፈላጊነት ፣ ስለዓላማው ፣ ስላጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ የተዘጋጀ ሰነድ በማቅረብ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን በማንሳት  ውይይት ተካሂዷል።

የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እና የስ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶረት በ2017 ዓ.ም በተደረገ ምዘና በከተማው ውስጥ ካሉ  ተቋማት ጋር በመወዳደር ባስመዘገቡት ስኬትና የላቀ አፈፃፀም  "ዕውቅና በላቀ ውጤት " በሚል ርዕስ የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ዳይሬክቶሬቶቹ ለስኬት ብቁ ያደረጉ ዋና ዋና ተግባራትን የሚገልፅ ሰነድ በማቅረብ ለዚህ ስኬት የበቁትን የሁለት ዳይሬክቶረቶች ዕውቅናና የመስጠትና ሰርተፍኬት የማበርከት መርሀ-ግብር ተከናውኗል።

በማጠቃለያው ላይ የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ለሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች እንኳን ደስ አላችሁ መልክት በማስተላለፍ የሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች እዚህ ደረጃ ላይ መድረስና እውቅና መሰጠቱ ለሌሎች በባለስልጣኑ ስር ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ለቀጣይ በላቀ ትጋት ስራዎች ሊሰሩ ይገባል የሚል መልክትን በማስተላለፍ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments