ባለስልጣኑ በከተማዋ በ83.8% የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ
ባለስልጣኑ በከተማዋ በ83.8% የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ
ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር ባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አደራሽ የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን በመግለፅ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንፃር የደንብ ጥሰት በ83.8% መቀነሱን ገልፀዋል።
በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባሻገር በሰው ተኮር ተግባራት ፣ በአቅመ ደካማ በቤት እድሳት፣በደም ልገሳ ፣ በችግኝ ተከላ እና ማዕድ የማጋራት በርካታ ስራዎች በመስራት በሩብ ዓመቱ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በሪፖርቱ የደንብ ጥሰቶችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር እርምጃ ከመውሰድ አንፃር ፣ ከኢንሸቲብ ስራዎች፣ከግንዛቤ ፈጠራ አና ከመልካም አስተዳደር አንፃር የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ተመላክተዋል።
በሩብ አመቱ ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ ከከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለከተማው ገቢ በማድረግ ለከተማው ልማት እንዲውል መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።
በግምገማው የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ መነሻ በማድረግ በቡድን በመከፋፈል ከመልካም አስተዳደር ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከብልሹ አሰራር ፣ የደንብ ጥሰቶችን ከመቀነስ እና ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተወሰዱ መፍትሔዎች ላይ በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች አወያይነት ሰፊ ውይይት ተደርጎል።
በውይይት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል
በመጨረሻም የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን በተለይ የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በትኩረት እንዲሰራና በካዮቹ ተጠያቂ እዲደረጉ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገበው ፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments