ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 2,592,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 2,592,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ
5/02/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻና ኬሚካል የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን መቅጣቱ አስታውቋል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ኢትዮ ሌዘር ፋብረኢካ ኬሚካል ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 800,000 ብር ፣8 የመኖሪያ ቤትና 1 ድርጅት ባመነጩት ቆሻሻ አወጋገዳቸው ደንብን በመተላለፉ ወንዞች በመበከላቸው በድምሩ 592,000/አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ተቀጥተዋል።
በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ረጲ ኮምዶሚኒዮም እና ግራር ሆቴል ፍሳሽ ቆሻሻን ከወንዝ በማገናኘታቸው በድምሩ 600,000 ብር፤በቂርቆስ ክ/ከተማ ዲሊኦፖል እንተርናሽናል ሆቴል 300,000 ብር ሲቀጣ በጉለሌ ክ/ከተማ አቶ ሙሉጌታ መንጋ እና አቶ ናትናኤል ገበያው ድርጅት 300,000 ብር ብር ተቀጥተዋል።
በባለስልጣኑ ከዚህ በፊት ለህብረተሰቡ ሰፊ ግንዛቤ እየፈጠረ የመጣ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የደንብ መተላለፍ በፈፀሙ ግለሰቦችን እና ድርጅቶች እርምጃዎችን በደንብ ቁጥር 180 /2017 መሰረት በድምሩ 2,592,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ) ብር ቀጥቷል።
ባለስልጣን መረጃ በመስጠት የአካባቢ ብክለት መከላከል እንዲቻል የጠቆሙትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስቧል:
በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments