የባለስልጣኑና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በሁለቱ ተቋም ጠቅላላ ካውንስል ተገመገመ::

የባለስልጣኑና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም  በሁለቱ ተቋም ጠቅላላ ካውንስል ተገመገመ::

           ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም
              አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት የማእከል አመራሮች በተገኙበት  በደንብ ማስከበር ባለስልጣን መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የግምገማ መድረክ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመክፈቻ  ንግግራቸው በሩብ አመቱ መጀመሪያ ዓለም አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ የሆኑት የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማከናወን መቻሉ የሁለቱ ተቋማት ጥምር ውጤት መሆኑን በማንሳት ከ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በመነሳት ለቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች መዘጋጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በግምገማው ላይ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ሰነድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል አድማሱ ተክሌ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።

በሪፖርቱ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ተቋማቱ ከተሰጣቸው ተልዕኮ ጋር በጥምረት በማያያዝ ክፍተቶችን በመለየት ለ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ እንደግብአት በመጠቀም በ1ኛ ሩብ አመት ተፈጻሚ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸው በሪፖርቶቹ ተገልጿል።

ከሪፖርቶቹ በመነሳት የተቋማቱ አመራሮች ከተቋም ግንባታ አንጻር ስለሚገኙበት ደረጃ፣ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ከመግታት አንጻር እየተሰሩ ስለሚገኙ ተግባራት እና ሌሎች በሂደት ላይ ስለሚገኙ ስራዎች የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳትና የመፍትሄ ሀሳብ በማቅረብ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በግምገማዊ ውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ 2017 በጀት ዓመት ሁለቱም ተቋማት ስኬትን ያስመዘገብንበት ዓመት መሆኑ የተለየ መነቃቃት የመጣበት ነው ያሉት ኃላፊው በ2018 በጀት ዓመትም ይህን ስኬት አስቀጥሎ መሄድ ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከቀረበው የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እንደ ክፍተት የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብአት በመውሰድ በቀጣይ በላቀ መነሳሳት ውጤታማ ስራዎችን የምንሰራበት መንገዶች መፍጠር እና እንደክፍተት ለታዩት ነጥቦችም አዳዲስ አሰራርና የመፍትሄ ሀሳብ በመዘርጋት ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ በግምገማዊ ውይይቱ ማጠቃለያ ተመላክቷል።

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  ለቀጣይ የትግበራ መርሀ-ግብር የሚሆን ቀጣይ ስራ አቅጣጫ በመስጠት ግምገማዊ ውይይቱ ተጠናቋል።

ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments