የባለስልጣኑ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸሙ ከሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር እየገመገመ ነው
የባለስልጣኑ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸሙ
ከሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር እየገመገመ ነው
06/02 /2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር እየገመገመ ይገኛል።
መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የተከፈተሲሆን የሁለቱ ተቋማት ሪፖርት ቀርቦ እንደሚገመገም ተመላክቷል።
ዝርዝር ዜናውን መድረኩ እንደተጠናቀቀ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments