ከተማችን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ሰላምና ጸጥታ...

image description
- In code inforcement    0

ከተማችን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ሰላምና ጸጥታዋ የተጠበቀ እንድትሆን የቅንጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።

ከተማችን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ሰላምና ጸጥታዋ የተጠበቀ እንድትሆን የቅንጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።

                06/02/2018 ዓ.ም
               **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር  የውይይት መድረክ አካሂዷል ።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በከተማው የተካሄዱ አለም አቀፍ ስብሰባዎች እና በአደባባይ የተከበሩ የሃይማኖትና ህዝባዊ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁለቱ ተቋማት የጸጥታ ሀይሉን በማቀናጀትና በማስተባበር ያከናወኑት ውጤታማ ተግባር በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከወንጀል መከላከልና መቀነስ ስራዎቻችን ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ውጤታማ የሆነ ስራዎች መሰራት መቻሉን ማህበረሰቡ የደንብ ማስከበር አጋዥ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስራዎችን አጠናክሮ በመሰራት የደንብ መተላለፍ በከተማችን እየቀነሰ መምጣቱን ኃላፊዋ ተናግረዋል ።

አክለውም በቀጣይ በከተማችን የሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የማህበረሰብና የፀጥታ መዋቅርን በማቀናጀት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ግንዛቤ መስጠት ስራዎች ተጠናክረው መሰራት አለባቸው ብለዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ውጤታማ የሆኑ አፈፃፀሞች የተገኙት ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋቱ ስራዎችን በዕቅድ መሠረት ማከናወን በመቻሉ መሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም በቀጣይ ከተማችን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ሰላምና ጸጥታዋ የተጠበቀ ውብ ጽዱ እንድትሆን የቅንጅት ስራዎችን በማጠናከር በክፍተት የታዩ ጉዳዮችን ዕቅድ በመከለስ የተሻለ ስራ ለማከናውን ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮን የ2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የእቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል ።

ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ ሠላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት እና የተፈጸሙ ድርጊቶችን ሳይባባሱ በቅንጅት በመከላከል የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን በሪፖርቱ ተገልጿል ።

የባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል ።

ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ እስከአሁን ባለው ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በስራ አፈጻጸም ግምገማው ሰፊ የሆነ ውይይት በማድረግ የተሳተፉ አመራሮችና ዳይሬክተሬቶች በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያየትና ጥያቄዎች አቅርበው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የቀጣይ ስራ አቅጣጫ በመስጠት ግምገማዊ ውይይቱ ተጠናቋል።።

ዘገበው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments