ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 820,000(ስምንት መቶ ሀያ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 820,000(ስምንት መቶ ሀያ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ
6/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን መቅጣቱ አስታውቋል።
ባለስልጣኑ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻ ከድሬኔጅ ጋር አገናኝቶ የለቀቀ ቱሉዲምቱ ማህበር ቤት 300,000 ብር ተቀጥቷል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት አሳማ እርባታ ድርጅት በካይ ፍሳሽ ቆሻሻን ከጎርፍ መውረጃ ቦይ ወደ ወንዝ በማገናኛት 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል።
በእለቱ በደንብ ቆሻሻን በአግባብ አለመያዝና በአይነት ባለመለየትና ወደ ወንዝ በመጣል ደንብ የተላለፉ ግለሰቦች 120,000 ( አንድ መቶ ሃያ ሺህ) ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት እርምጃ እርምጃ ተወስዷል።
ተቋሙ መረጃውን ለባለስልጣኑ በመስጠት የአካባቢ ብክለት መከላከል እንዲቻል የጠቆሙትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስቧል:
በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments