39ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ው...

image description
- In code inforcement    3

39ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው ብሔራዊ የመካከለኛ ዘመን 2017-2020 የገቢ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የታክስ ሥርዓቱን ለማዘመን እና ለግል ኢንቨስትመንቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የታለመ ሲሆን አጠቃላይ የታክስ ፖሊሲዎችን እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን እንዲሁም ማሻሻያዎችን ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡ ሰትራቴጂው ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተደርጎ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ውሳኔ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments