ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 1,750,000(አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 1,750,000(አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ
10/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 1,750,000(አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታውቋል።
ቅጣቶቹ በቄርቆስ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ወደ ወንዝ በካይ ፍሳሾችን በመልቀቁ በድምሩ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር፣ በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 400,000/አራት መቶ ሺህ/ ብርተቀጥተዋል።
በተጨማሪም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወንዝ በመበከል ፋፋ የምግብ ፋብሪካ 400,000/አራት መቶ ሺህ/ ብር በጉለሌና በየካ ክፍለ ከተማ የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 150,000(ሀምሳ ሺህ) ብር እና 200,000(ሁለት መቶ ሺህ) ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
ባለስልጣኑ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም እያሳሰበ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments