ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስ...

image description
- In code inforcement    0

ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ውይይት ተካሄደ

ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ውይይት ተካሄደ   
         
                10/02/2018 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለአመራሮች፣ ለባለሙያዎችና ኦፊሰሮች የአጭር ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት የባለስልጣኑ እና የዩኒቨርስቲው አመራሮች ውይይት አካሄዱ ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አመራሩና ባለሙያው የአፈጻጸም አቅሙ ጠንካራ እንዲሆን የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ እና መልካም አስተዳደርን በመረዳት የደንብ ማስከበር አገልግሎቶችን በሚገባ እንዲሰጡ ወቅቱን የጠበቀ ስልጠና ግንዛቤን ለማሳደግ አስፈለጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው  ስራቸዉን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የሚችሉበትን በቂ ዕውቀት የሚያገኙበት ስልጠና ልምድና እውቀቱ ባላቸው አሰልጣኞች እንደሚያዘጋጁ  ገልፀዋል፡፡

አክለውም ዩኒቨርሲቲው ለሰልጣኞች አመቺ ቦታ እንዲሁም ከተቋሙ ጋር ተዛማጅነት ያለው ስልጠና ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች እና ኦፊሰሮች ስልጠና የተዘጋጀ መነሻ ሀሳብ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአመራር ስልጠና አቅም ግንባታ ማዕከል መምሪያ ኃላፊ  ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

በተቋሙ ተመድበው የሚሰሩ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ወቅቱን መሰረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት የእውቀት ፣ክህሎት ፣አመለካከት ፣ የስነምግባር እና የስራ አፈጻጸማቸውን የላቀ በማድረግ ስለተቋማቸውና ስለሚሰጡት አገልግሎት ሁኔታ ልዩ ባህሪ በቂ ግንዛቤ ይዘው የህዝብ አገልጋይነት ስሜትን ተላብሰው የተቋሙን አላማ ለማሳካት በቀጣይ የሚሰጠው ስልጠና ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው በመድረኩ ተገልጿል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments