ባለስልጣኑ ለተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል አልባሳት እና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።
ባለስልጣኑ ለተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል አልባሳት እና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።
19/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ "ለአረጋውያን ደህንነትና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን የአረጋውያን ቀን አስመለክቶ በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኘው ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል አልባሳት እና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ስጦታወን ያበረከቱት የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እንዳሉት ከዚህ ቀደም ተቋሙ ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ የተለያዩ የአረጋውያ ማዕከላትን መጎብኘትና ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም የአቅመ ደካማ ቤቶችን መገንባትና ማደሳቸውን፣ ማዕድ ማጋራትና ደም ልገሳ በጎ ተግባራት ላይ በስፋት መስራታቸውን አስታውሰዋል።
በዛሬው ዕለትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለባለስልጣኑ ያቀረበለትን ጥሪ በመቀበል የባለስልጣኑን ሰራተኞች ጭምር አስተባብሮ ለተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል አልባሳትና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ማስረከባቸውን ገልጸው፤ ተቋሙ እያከናወነ የሚገኘውን የተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎችን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉደይ ቢሮ የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው ቢሮው አረጋውያን በስነ ልቦ እና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ተግባራቶችን ከማከናወን ጎን ለጎን የተለያዩ ባለሀብቶችን በማስተባበር ቋሚ የምገባ ማዕከል ጭምር እንዲገነቡ በማድረግ የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ፤ቢሮው ያቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ ለሰጠው ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምስጋናና የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክተዋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments