ባለስልጣኑ በእሳት እና አደጋ ስጋት መመሪያ ደን...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በእሳት እና አደጋ ስጋት መመሪያ ደንብ 163/2017 እና የአተገባበር ማኑዋል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በእሳት እና አደጋ ስጋት መመሪያ ደንብ 163/2017 እና የአተገባበር ማኑዋል ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

                20/02/2018 ዓ.ም
              **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በመተባበር በእሳት እና አደጋ መመሪያ ደንብ ቁጥር 163/2017 እና የአተገባበር ማኑዋል ዙሪያ ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ አመራሮች ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ፉፋ ተቋማት የደንብ መመሪያው አተገባበር ላይ በቂ ግንዛቤ አግኝተው ተፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዲችሉና መመሪያውን ለማስተግበር የአተገባበር ማንዋሉ ላይ ተሳታፊዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ስልጠናው ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል ።

የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ መከላከል ፣ ቁጥጥር ፣ ፍሳሽና ብቃት ማረጋገጥ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 163/2017 እና የአተገባበር ማንዋል ለአመራሮች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የብቃት ማረጋገጥ ቡድን መሪ ተወካይ አቶ ጋሻውን ካሳዬ በዝርዝር ቀርቧል።

ኮሚሽኑ ከባለስልጣኑ ጋር በተፈራረሙት የስራ መግባቢያ የስምምነት ሰነድ መሰረት በአዋጅ ፣ በመመራያ እና የአተገባበር ማኑዋል ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠትና ወደ ተግባር በመግባት በከተማችን ውስጥ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ከአሰራር ውጪ በሚሆኑ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በህግ ኃላፊነት ከተሰጠው ተቋም ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር ያለውን ቅንጅት ለማጠናከር ያለመ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል ።

ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመመሪያው አተገባበር ላይ ፍቃደኛ የማይሆኑ፣ተቋማቸውን ለማስፈተሽ ፍቃደኛ የማይሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ከኮሚሽኑ መረጃ ሲደርሰው የህግ ማስከበር ስራ ይሰራል እንዲሁም በማንኛውም መተላለፊያ መንገድ ላይ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችን መሳሪያዎችን በቀላሉ መተላለፍ እንዳይችሉ የሚያግዱ ተግባራትን የፈጸመ ግለሰብ ወይም ተቋም ላይ የህግ ማስከበር ስራ በመስራት ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው በሰነዱ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ሰፊ ውየይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments