"ለስማርት ሲቲ ለመገንባት ስማርት ባለሙያ መፍጠር አስፈላጊ ነው" አቶ ተስፋሁን አሉላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጽ/ቤት ኃላፊ
"ለስማርት ሲቲ ለመገንባት ስማርት ባለሙያ መፍጠር አስፈላጊ ነው" አቶ ተስፋሁን አሉላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጽ/ቤት ኃላፊ
25/02 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለማዕከሉ ባለሙያዎች እና ለ11ዱም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የITና ኮምፒውተር ሳይንስ ምሩቃን ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊስሮች በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለማስጀመር የመስክ አስተዳደር /Field managmet system/ ስልጠና ተሰጠ ።
በስልጠና መክፈቻው የባለስልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ባለስልጣኑ ሙሉ ሙሉ ውደ ቴክኖሎጂ ለማስገባት በርካታ ሰራዎች በመስራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙን ለማዘመን ከወረቀት ንክኪ ነጻ ፣ ቀልጣፋና ውጤት ተኮር ተግባራትን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መረጃዎች በማስደገፍ እንደሚከናወን ገልጸዋል ።
አክለውም ለስማርት ሲቲ ስማርት ባለሙያ አስፈላጊ በመሆን ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል የመረጃ አያያዝ ስርዓትና የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት በመዝርጋቱ ስራ ለመጀመር ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት መከታተል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ።
ተቋሙን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀት የኔትወርክ መሰረት ልማት ስራዎችን ዘርግቶ በማጠናቀቅ በራስ አቅም የተሰሩ ሶፍትዌሮችን ወደ ተግበር ለማስገባት ስልጠናው መጀመሩ የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ካሳሁን ተናግረዋል ።
የመስክ አስተዳደር /Field managmet/ ስልጠና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በመጡ የሶፍትዌር ኢንጅነር ባለሙያ አቶ አማኑኤል መኮንን እና የሶፍትዌር ፕሮግራም ባለሙያ አቶ ሀብታሙ ጴጥሮስ ተሰጥቷል ።
ተቋሙ የሚያከናውነውን ተግባራት በአንድ
ሲስተም ውስጥ በማካተት ወጥ የሆነ መረጃ አያያዝ ስርዓትን በመዘርጋት ከወረቀት ንክኪ የጸዳ ምቹ እና ቀልጣፋ ስራ ለማከናወን የበለጸገው ስፍትዌር ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል ።
ሰልጠናውን በየደረጃው ያሉ ሁሉም የባልሰልጣኑ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በቀጣይ ቀናት እንደሚወስዱ የስልጠና አስተባባሪዎች ተናግረዋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments