የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ በደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ በደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሄደ
02/03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመገኘት በወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም ፣የተከናወኑ ተግባራትና ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሂዷል::
የከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ኦልያድ ቡልታ በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙሪያ ለህብረተሰቡ የተደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች መከናወኑን ማየት መቻሉን ገልፀው በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
አክለውም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ወደ ህብረተሰቡ በአግባቡ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች በቂ ግንዛቤ እያገኙ መሆኑ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ዘርፍ የመጣው ቡድን ተቋሙ በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙሪያ ያከናወናቸውን ስራዎች እንዲሁም ለግንዛቤ የተዘጋጁ ሰነዶቹንና ግንዛቤ የተፈጠረላቸውን አካላት የሚያሳዩ ሰነዶቹን ምልከታ አድርገዋል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments