ባለስልጣኑ ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሴፍቲ ታንከር በማዘጋጀት ወደ የወንዝ ብክለት ማስቆሙ ገለፀ
ባለስልጣኑ ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሴፍቲ ታንከር በማዘጋጀት ወደ የወንዝ ብክለት ማስቆሙ ገለፀ
03/03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ ወደ ወንዝ በካይ ፍሳሾችን ወደ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ እንዲፈስ በማድረጉ በተቀመጠለት ቀነ ገደብ መሰረት ችግሩን መቅረፍ መቻሉን ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው የመስክ ምልከታ ማረጋገጡ አስታውቋል ።
ባልስልጣኑ ህብረተሰቡና ተቋማት ወንዝና የወንዝ ዳርቻ እንዳይበክሉና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም እያሳሰበ አጥፍተው ሲገኙ ከስህተታቸዉ በመታረም በተቀመጠላቸው ቀነ-ገደብ መሰረት እንዲያስተካክሉ አሳስቧል።
ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ በተቀመጠለት ቀነ ገደብ መሰረት ችግሩን በማስተካከሉ ባለስልጣኑ እያመሰገነ ሌሎችም ተቋማትና ግለሰቦች ችግራቸው እንዲያስተካክሉ የተነገራቸው ተቋማት ከካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ በመማር የከተማው ወንዞች ለመዝናኛ አገልግሎት እንዲውሉ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገጿል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments