በተቋማዊ ስታንዳርዳይዜሽን ማንዋል አተገባበር ዙ...

image description
- In code inforcement    0

በተቋማዊ ስታንዳርዳይዜሽን ማንዋል አተገባበር ዙርያ ላይ ስልጠና ተሰጠ

በተቋማዊ ስታንዳርዳይዜሽን ማንዋል አተገባበር ዙርያ ላይ ስልጠና ተሰጠ

          ህዳር 4/2018 ዓ.ም
          **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በተቋማዊ ስታንዳርዳይዜሽን ማንዋል አተገባበር ዙርያ ለባለስልጣኑ የማዕከል ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።

ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት ያስመዘገበው ውጤቱ አስጠብቆ ለመሄድ የስታንዳርዳይዜሽን ትግበራዎችን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን እና  ለዚህም    የሁሉም ባለሙያ ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር  አስፈላጊ መሆኑን  በስልጠናው የተገኙት  የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ገልጸዋል ።

አማካሪዋ አያይዘውም ባለስልጣኑ ከኢኖቤሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር  በመተባበር የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን  በማስተግበር ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

በተቋማዊ ስታንዳርዳይዜሽን ማንዋል አተገባበር ዙርያ ላይ የተዘገጀውን ስልጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የስታዳርዳይዜሽን የአፈፃፀም ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በወ/ሮ ሰላማዊት ይመር ተሰጥቷል።

በስልጠናው  የስታንዳርዳይዜሽን ምንነት፣ የአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ደረጃዎች ፣ ስለ ሂደት ስታንዳርዳይዜሽን ፣ የአፈፃፀም ስታንዳርዶይዜሽን፣ ሰለ ሰው ሀብት ልማት ስታንዳርዳይዜሽን ፣ ስለ ግዠና ንብረት አስተዳደር ስታንዳርዳይዜሽን፣ ሰለ መረጃ ስታንዳርዳይዜሽን፣ በቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ስታንዳርዳይዜሽን እና በተቋማዊ ስታንዳርዳይዜሽን ዙርያ በስፋት በጥልቀት በማብራራት ተሰጥቷል ።

ሰልጠናው ሳቢና ማራኪ ለአሰራርም  የሚጠቅም በመሆኑ  ስልጣኞች በባኙት ግንዛቤ ላይ ማንዋሉን በጥልቀት በማንበብ ወደ ስታንዳርዳይዜሽን ትግበራ መግባት እንደሚችሉ  ሰልጣኞች አስተያየት ለማወቅ ተችሎል።

መረጃው ፦ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments