በከማችን የሚስተዋሉ የህገ-ወጥ እንስሳት እርድ እና ዝውውር በጤና ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በከማችን የሚስተዋሉ የህገ-ወጥ እንስሳት እርድ እና ዝውውር በጤና ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
05/03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት እና አርሶአደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ጋር በመተባበር የህገወጥ እንሳሳት እርድና ዝውውር በተመለከተ የሶስቱ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ከስጋ ቤት ባለቤቶችና የልኳንዳ ቤት ነጋዴዎች ማህበር አባላት ጋር የውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ደንብ ማስከበር ከተማችን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለነዋሪዎቿ ምቹ ለእንግዶቿ ተስማሚ እንድትሆን በርካታ ተግባራት እያከናወነ የሚገኝ መሆኑ ገልፀዋል።
በተለይ አልፎ አልፎ በከማችን የሚስተዋሉ የህገወጥ እንስሳት እርድ እና ዝውውር በጤናና በኢኮኖሚ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ በጋራ በመከላከል ለህብረተሰባችን ደህንነቱ የተረጋገጠ ጤናማ የምግብ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
አክለውም በህገወጥ እንስሳት እርድ እና ዝውውር ላይ በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙና በግንዛቤ መስተካከል ያልቻሉ ደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወሰደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ጤንነቱ የተጠበቀና ጥራቱ የተረጋገጠ ስጋዎችን ለህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ እና ከቄራ ውጪ የሚፈጸሙ ህገዋጥ እርድን ለመከላከል ከሚለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በከተማችን ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ሱሉ ተናግረዋል ።
ለጤና አስጊ የሆኑ ምርመራ ሳይደረግባቸው በህገወጥ የሚከናወኑ የእንስሳት እርዶች ጤናን የሚያውኩ በመሆናቸው ሁላችንም የበከሉላችንን በመወጣት መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
በህገወጥ እንስሳት እርድና ዝውውር ዙሪያ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክተር ወ/ሮ ስርካለም ጌታሁን ቀርቧል ።
በአራት ወራት ውስጥ 138 ህገወጥ የእንስሳት ዝውውር እርድና ሽያጭ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን በሰነዱ ተገልጿል ።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት እና አርሶአደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን በህገወጥ እርድና የአንስሳት ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበዋል።
የአዲስ አበባ አርሶአደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ዶር ጸጋ ለማ ህገ ወጥ እርድ ቁጥጥር ተግባራን በማጠናከር የህብረተሰቡን ጤና በመጠበቅ የበለጸገ ሀገርና ህብረተሰብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።
በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ሰፊ ውየይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments