የባለስልጣኑ የመጀመሪያ ዙር የወታደራዊና የስነምግባር ስልጠና ሰልጠኝ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ወደ ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ማሰልጠኛ በሰላም ገብተዋል
የባለስልጣኑ የመጀመሪያ ዙር የወታደራዊና የስነምግባር ስልጠና ሰልጠኝ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ወደ ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ማሰልጠኛ በሰላም ገብተዋል
07/03/2018 ዓ.ም
**ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የመጀመሪያ ዙር የወታደራዊና የስነምግባር ስልጠና ሰልጠኝ አመራሮች እና ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰላም ደርሱ።
ወደ ማሰልጠኛው እንደደረሱ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብና አስተባባሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ደንብ ማስከበር አቅሙን በየጊዜው በማሳደግ ስራዎቹን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ወቅቱን የጠበቀ ስልጠናዎችን ለአመራሩ እና ሰራተኛው በመስጠት የአቅም ግንባታን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።
አክለውም የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል የግቢውን ህግና ደንብ በማክበር መላው ሰልጣኝ ስልጠናውን በቂ እውቀት አግኝቶበት ማጠናቀቅ እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአመራር ስልጠና አቅም ግንባታ ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው ለሠልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልክታቸውን አስተላልፈው ሰልጣኞች ስልጠናውን ንቁ ሆነው በትኩረት መውሰድ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ።
የንድፈ ሀሳብ እና በወታደራዊ ሥልጠናው በነገው እለት የባለስልጣኑ እና የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመክፈቻ ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገልጿል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments