“በስነ ምግባር የታነፀና በህዝብ የታመነ አገልጋይ ለመገንባት እንደሚሰራ ተገለፀ
“በስነ ምግባር የታነፀና በህዝብ የታመነ አገልጋይ ለመገንባት እንደሚሰራ ተገለፀ
8/03/2018 ዓ.ም
ሰንዳፍ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለአመራሮች እና ለፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰነንዳፋ በሚገኘው በኢትዮጲያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ተቋም ለመስጠት የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የማስጀመሪያ መርዓ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ2017 ያገኘነውን ድል ለማስቀጠል እና የላቀ አፈፃፀም ለማምጣት በተቋሙ የሚገኙ አመራሮች እና ኦፊሰሮች በተከታታይ ስልጠና ማብቃት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው፤ ሰልጣኝ ኦፊሰሮችና አመራሮች በዪኒቨርስቲው የሚሰጡትን ስልጠናዎች በንቃት በመከታተል በአገልጋይነት መንፈስ ታንፀው እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዪኒቨርስቲ የአቅም ግንባታ እና ስልጠና መመሪያ ሀላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው ዩኒቨርስቲው ላለፍት 78 ዓመታት በሀገራችን ውስጥ ለሚገኙ ፖሊሶች በርካታ ስልጠናዎችን እንዲሁም የምርመራ ተቋም በመሆን እያገለገለ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት ከተማችን አዲስ አበባ የደረሰችበትን ስልጣኔ ለማስቀጠል እየሰራ ነው ይህንንም ለማዘመን አስፈላጊ የሚባሉ ርዕሶችን በመምረጥ ዩኒቨርስቲው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግረዋል።
የባለስልጣኑ የቅድመ መከላከል እና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተቋማችንን ጊዜውን የዋጀ እና ከተማችንን የሚመጥን በባህሪ፣በቴክኖሎጂ፣በስነምግባር የታነፁ ኦፊሰሮች ለማፍራት የተለያዮ ርዕሶችን በመምረጥ በንድፈ ሀሳብ እና ወታደራዊ ስልጠናዎችን ለመስጠት ከኢትዩጵያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ ጋር በጋራ ዝግጅታቸውን ገልፀው የዕለቱ የመክፈቻ መርሀ-ግብር ተጠናቋል።
ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments