ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ቀን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ቀን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
9/3/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት!" በሚል መሪ ቃል ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀንን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ከፍተኛ ሀላፊዎች እና መላው የማዕከል ሰራተኞች በተገኙበት የፓናል ውይይት በማድረግ በዓሉ ታስቦ ውሏል።
በዓሉን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ቋንቋዎች የሚነገርባት የብዝሀ ቋንቋ እና የብዝሀ ሀይማኖት ሀገር ብትሆንም በአብሮት በአንድነት እርስ በእርስ በመተሳሰብ በጋራ በመሆን ብሄራዊ አንድነቷን አስጠብቃ መቆየቷን ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ ለ20ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሀገራችን ወደ ብልፅግና እየገሰገሰች ባለችበት በዚህ ጊዜ የሚከበር በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በዓሉ ህዳር 29 በሀገር አቀፍ ደረጃ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እንደሚከበር አውስተዋል ።
``ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት!" በሚል መሪ ቃል ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ በባለስልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ አቅርበዋል።
በሰነዱ በዲሞክራሲ ምንነት ፣ በዲሞክራሲ እና በፌደራሊዝም መካከል ያለው ልዩነት አና አንድነትን ፣ በፌደራሊዝምና ፌደሬሽን ስላለው አንድነት አና ልዩነት እና እንድሁም አንድ ሀገር ፌደራል ስራዓት አለው የሚባለው መቼ ነው በሚሉ ይዘቶች ላይ ሰነዱ ቀራቧል።
በቀረበው ሰነድ ዙርያ በባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እና በባለስልጣኑ ጽ/ኃለፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ አወያይነት ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው በመድረኩ በተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቶበት የፓናል ውይይቱ ተጠናቋልል።
መረጃው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments