በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች...

image description
- In code inforcement    0

በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ ተወሰደ

በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ ተወሰደ

               15/03/2018 ዓ.ም
               **አዲስ አበባ**   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በትላንትናው ዕለት በቀን 14/03/2018 ዓ.ም በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱ አስታወቀ።

ድርጊቱ የከተማው ገፅታ የሚያበላሽና ልማቱ ለታለመለት አላማ እንዳይውል የሚያደርግ በመሆኑ ጥፋቱን ፈፅመው የተገኙ የኮረደሩ ልማቱ መዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን ወደ በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂ በማድረግ ጉዳዩ እስኪወሰን ካፌው መታሸጉ ተገልጿል።

ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ  በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ መገልገልና መጠቀም እንደሚገባም አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ ደንብ የተላለፈው የመንግስት ይሁን የግል  ድርጅቶች እና ግለሰቦች ያለዩነት በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም  አስታውቋል ።

ባለስልጣኑ ጥቆማውን የሰጠው የህብረተሰብ ክፍል እያመሰገነ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች  ጥቆማ  በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments