ባለስልጣኑ '''ትውልድን በስነምግባር ተቋምን በአሰራር !'' በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የፀረ_ሙስናን ቀን አከበረ።
ባለስልጣኑ '''ትውልድን በስነምግባር ተቋምን በአሰራር !'' በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የፀረ_ሙስናን ቀን አከበረ።
15/3/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአለም ለ22 ጊዜ በሀገራችን ለ21 ጊዜ የሚከበረውን የፀረ_ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እና የማዕከል ሰራተኞች በተገኙበት የፀረ ሙስና ቀንን አከበረ።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ 1100 የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር ታንፀው እና በአካል በቅተው የአሰራር ክፋተቶችን እንዲያስተካክሉ ወደ አፋር አዳይቱ ማሰልጠኛ ማዕከል መላካቸውን ገልጸዋል ።
ሻለቃ ዘሪሁን የሙስና ቀንን ስናከብር ከብልሹ አሰራርን በመታገል በተለይም በንብረት አጠቃቀም ፣ በግዢ አገልግሎት አሰጣጥ ፣ በፋይናንስ አሰራር እና የመንግስትን የስራ ስዓት ለሰራ ማዋልን በመሳሰሉት ላይ ጥንቃቄዎች ሊደረግባቸው እንደሚገባና በሙስናና በብልሹ አሰራር ዙርያ እርስ በእርስ በአቻ ፎረም መተጋገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የፀረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱሞ ስለ ብልሹ አሰራር እና ሙስና የሰነ ምግባር መርሆች ፣ ስለ ስነምግባር መለኪያዎች ፣ ሰለ ፀረ ሙስና የህገ ማዕቀፎች ፣ የሙስና ወንጀል ስለሚያስከትለው ጉዳት ፣ የሙስና መከላከያ ስልቶች እና በሙስናን ትግል ምቹ ሁኔታ እና ተግዳሮቶች በመሳሰሉት ዙርያ ስልጠናው ተሰጥቷል።
በመጨሻም በተቋሙ ስራተኞች የጥያቄና መልስ ውድድር በማድረግ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ምለሽ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነዉ ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments