ባለስልጣኑ የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ገመገመ ።
ባለስልጣኑ የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ገመገመ ።
16/03/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ **
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከእቅድ አንፃር የተከናወኑ በርካታ የደንብ መተላለፎችን የመከላከል እና የመቆጣጠር ተግባራት እንዳሉ ጠቅሰው፤ እነዚህ ተግባራት በህብረተሰቡ ተሳትፎ የታገዙ እንደነበርና በቀጣይም ከጎናችን በመቆም በጋራ ሆነን ደንብ መተላለፍን እና ህግ የማስከበር ተልዕኳችንን አጠናክረን በማስቀጠል ራዕያችንን ከግብ ማድረስ ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል።
ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በሙያዊ ስነምግባርና ዲስፕሊን የታነጹ ከብልሹ አሰራር የጸዳ የተሰጠውን ተልዕኮ በኃላፊነት መወጣት የሚችል የደንብማስከበር አመራርና ኦፊሰር ለመገንባት ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የንድፈ ሀሳብ እና በወታደራዊ ሥልጠና እይተሰጠ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
አክለውም የደንብ መተላለፎችንና ተያያዥ ወንጀሎችን ለመቀነስ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን ወደ ህብረተሰቡ ተደራሽ በሚሆን መልኩ በተለያዩ መንገዶች እየተሰጡ እንደሚገኙና የሪፎርም ስራዎቻችንን በማጠናከርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን በማከናወን ከተማችን የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ውብና ጽዱ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በሪፖርቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ክፍተቶች ለመፍታት የተከናወኑ መፍትሔዎች ተካተውበታል።
በሪፖርቱ ባለስልጣኑ ከአስራ አራት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 14 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ገንብቶ ለባለቤቶቻቸው ማስረከቡ ተገልጿል
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments