ባለሥልጣኑ በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ አካላትን አስጠነቀቀ
ባለሥልጣኑ በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ አካላትን አስጠነቀቀ
16/03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ትውልድን የሚያመክኑ አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ።
ባለስልጣኑ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በአዋኪ ድርጊት ገንዘብ ለማግኘት ተሠማርተው በነበሩ ግለሠቦች ላይ ደንብ ማሥከበር ባለስልጣን በስራው ኦፕሬሽን 98 የሽሻ ማስጨሻ እቃዎች ላይ እርምጃ እንዲወገዱ ተደርገዋል።
ለትውልድ ገዳይ የሆነውን አዋኪ ድርጊት በተለይ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተለያዩ ሱስ የሚያሲዙና ያልተገቡ ድርጊቶች እንዳይከናወኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ በቀጣይ በአዋኪ ድርጊት በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የደንብ ማስከበር ስራው አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፎች በነፃ ስልክ መስመር 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ መረጃዎች:-
https://linktr.ee/aacodeenforcement?utm_source=linktree_admin_share
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments