ባለስልጣኑ አመራርና ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሩን ለተሻለ ተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ የማጠቃለያ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ አመራርና ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሩን ለተሻለ ተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ የማጠቃለያ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ
16/03/2018 ዓ.ም
**ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዮንቨርሲቲ ጋር በመተባበር እያሰለጠነ የሚገኘውን የመጀመሪያዙር ነባር አመራርና ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለተሻለ ተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ ግምገማዊ ስልጠና ሲያካሂድ ውሏል።
በባለስልጣኑ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና በቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደ መስቀል ሲመራ የዋለው ስልጠና ዋነኛ ግቡ ሰልጣኝ አመራሮችና ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር ታንፀውና እራሳቸውን ለተልዕኮ ዝግጁ በማድረግ ህብረተሰቡን በብቃትና በታማኝነ ለማገልገል እንዲችል አቅሙን መገንባት እንደሆነ ገልፀዋል።
የስልጠና አሰጣጥ ሂደቱም ሰነድ የቀረበ ሲሆን፤ አመራር ና ኦፊሰሩ ለህብረተሰቡ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ምን ጠንካራ ጎን አለው፣ ደካማ ጎኑስ ምን ላይ ነው በተለይ በስነ ምግባርና በአገልጋይነት ዙሪያ ምን ይመስላል የሚሉት በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተመላክቷል።
ሰልጣኝ አመራርና ኦፊሰሮችም በቡድንና በጋራ ውይይቶች ሀሳቡን በማንሸራሸር ውስጣቸውን የተመለከቱበትና በስልጠናው ዝቅ ብሎ ህብረተሰቡን ለማገልገል ዝግጁ የሚያደርግ እውቀቶችን የቀሰሙበት እንደሆነ ገልጸዋል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments