ባለስልጣኑ የበጎ ተግባራት ስራዎቹ በገንዘብና በ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የበጎ ተግባራት ስራዎቹ በገንዘብና በጉልበት ድጋፍ በማድረግ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸ

ባለስልጣኑ የበጎ ተግባራት ስራዎቹ በገንዘብና በጉልበት ድጋፍ በማድረግ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸ

               17/3/2018 ዓ.ም
              **አዲስ አበባ**

አዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች የበጎ ተግባራት ስራዎቹ በገንዘብና በጉልበት ድጋፍ በማድረግ አጠናክሮ መቀጠላቸው ተገለጸ።

በባለስልጣኑ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት አመራርና ሰራተኞች ከምግባር በህይወት መርጃ ማህበር ጋር በመሆን ለአቅመ ደካማዎች ግለሰቦችን በማጠብ፣ ፀጉር የማስተካከል እና ከአባላቱ በተዋጣ ገንዘብ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የበጎ አድራጎት ማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ዳኛቸው አማረ የደንብ ማስከበር አባላት ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ለቀጣይም ሌሎች ተቋማት የእናንተን አርዓያ በመከተል ድጋፍ እንዲያደርጉ  ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት አመራሩና ኦፊሰሮች  በማስተባበር የዕረፍት ሰዓታቸዉን በመጠቀም በወረዳዉ ዙሪያ ለሚኖሩ አርሶ አደሮች በአጨዳ በማገዝ ሰብል በመሰብሰብ የማበረታታት ስራ መሰራቱን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች  ጥቆማ  በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ይጠቀሙ!

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments