ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእው...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

                  22/03/2018 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ከተቋሙ ውጪ የሆነ እንግዳ በመጋበዝ የተቋም ውጤታማነት በሚል ርዕስ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሳምንቱን ንቁ ሆነን ዉጤታማ ስራ ለማከናወንና በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን መልካም ምኞት በመለዋወጥ ያለንን እውቀት በማካፈል ምንማማርበትና  ልምድ የምንለዋወጥበት ነው በማለት አሁን ላይ እየተጠናከረ እየመጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

አክለውም በተቋማችን ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለና ዘመናዊ በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሰራተኞቹም ለስራ ተነሳሽነት ያለቸው መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የዕለቱ የወርቃማ ሰኞ እንግዳ የግል ከፍተኛ ተቋማት ማህበር ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ ተቋማዊ ዉጤታማነት ለፐብሊክ ሰርቪስ በሚል ርዕስ ለባለስልጣኑ አመራሮች ሰራተኞች የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል ።

በሰነዱ ተቋማዊ ውጤታማነት ከሲቪል ሰርቪስ አንጻር ምን እንደሚመስል ፣ ለተቋማዊ ውጤታማነት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ጉዳዮች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ መንገዶች በዝርዝር ቀርበዋል ።

ተቋማዊ ውጤታማነት አንድ ተቋም ያስቀመጣቸውን ግቦች በምን ያህል ደረጃ ማሳካቱ ፣ ለሰራተኞች ምቹ አከባቢ ስለመፍጠሩ እና የተገልጋዩችና የህብረተሰቡን ፍላጎት የማርካቱ አጠቃላይ የግምገማ ውጤት ማሳያና መገለጫ መሆኑን አቶ ተፈራ ገልጸዋል ።

አክለውም ተቋማዊ ውጤታማነት በተግባራዊ ጥረት እና በተቀናጀ ስራ የሚረጋገጥ መሆኑን ተናግረዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments