በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በህገወጥ እርድና እንሰሳት...

image description
- In code inforcement    0

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር የግንዛቤ ማስጨበጫ የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር የግንዛቤ ማስጨበጫ የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ
        
                   22/03/2018 ዓ.ም
                    አዲስ አበባ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በህገ-ወጥ እንሰሳት እርድና ዝውውር ላይ የሀይማኖት አባቶች፣አባ ገዳዎች ፣ሀደ ሲንቄዎች፣ሲቪክ ማህበራት፣ታዋቂ ግለሰቦች፣ የእድር መሪዎች፣የብሎክ አስተባባሪዎች፣ሴቶች፣ወጣቶች፣ ሰላም ሰራዊት፣የልኳንዳ ቤት ባለቤቶች በተገኙበት በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄና የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ።

መድረኩ በሀይማኖት አባቶች፣በሀገር ሽማግሌዎች እና አባ ገዳዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን በመድረኩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ እንደተናገሩት ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ለህብረተሰቡ በደንብ መተላለፎች ላይ ሰፊ ግንዛቤ እየፈጠረ መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለትም በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር ላይ ለህብረተሰቡን ግንዛቤ በመስጠት በጋራ በመስራትእንደሚገባ ገልፀዋል።

አክለውም  እራሳችንን ከተለያዩ በሽታዎች እና ጤንነቱ ያልተረጋገጠ ስጋዎችን በየወንዝ ዳርቻዎች ፣በየአካባቢያችሁ ጨለማን ተገን አድርጎ ባልተፈቀደ ቦታ ፣በግለስብ ቤቶች ከሚታረዱ ህገወጥ እርዶች ከመመገብ እንቆጠብ ሲሉ አሳስበዋል።

በእለቱ ህገወጥ እርድ ሲከናወን ከህብረተሰቡ የተደበቀ አይደለም ከዚህ ጋር ተያይዞ ደንብ ተላልፈው ሲገኙ  ጥቆማ በመስጠት እና ከተቋሙ ጎን በመቆም ደንብ መተላለፍን መቀነስ እና ማጥፋት እንደሚቻል ገልፀው ደንብ ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት ደንብና መመሪያው ባስቀመጠው መሰረት እርምጃ እንደሚወሰድበት ተገልጿል ፡፡

በመድረኩም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጌታሁን ኃብተ ማሪያም በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር ሰነዶችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ሰፊ የህዝብ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ከደንብ ማስከበር ጎን ለመስራት ተነሳሽነት መኖሩን ገልፀው  ከመድረኩ የተነሱትን ሀሳብና አስተያየት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ፣የደንብ መተላለፍ መከላከል እና ስልጠና ስራዎች አስተባባሪ ወ/ሮ ንፁህ ታጠቅ፣የስልጠና ቡድን መሪ አቶ ጌታሁን ኃ/ማሪያም በጋራ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ተጠናቋል፡፡

      በአዲስአለም ከፈለኝ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments