የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች የስራ ልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ
የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች የስራ ልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ
23/03/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራዎችላይ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ።
በልምድ ልውውጡ ላይ የትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት ስለ ተቋማቸው ተግባር እንዲሁም የስራ ክፍሉን መዋቅርና ዝርዝር ስራዎችን ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።
በልምድ ልውውጡ ወቅቱን የሚጠይቀው የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎችን በማዘመን የተሻለ የመረጃ ምንጭ መሆንእንደሚገባ ተገልጿል።
በተቋሙ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እየተተገበሩ ያሉ የህዝብ ግንኙነት፣የህትመት ውጤቶች ፣የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና የመረጃ አደረጃጀትና ተደራሽነት ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያና በመስጠት የስራዎች ምልከታ ተደርጓል ።
የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ማሳደግ ስራዎችን ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ ከፍተኛ ጠቀሜታ መኖሩንና ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት እና ለህብረተሰቡ ተደረሻ ሲደረግ ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ አቶ አበበ ገልጸዋል ።
የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ለተደረገላቸው የልምድና ተሞክሮ ማጋራት አመስግነው ከትምህርት ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣የመረጃ አደረጃጀት አና የሚዲያ ሞኒተሪንግ ተግባራትን የወሰዱትንም ልምድ ወደ ተቋማቸው በማምጣት የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች አጠናክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments