ባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን የህዝግንኙነት ስራዎቹን...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን የህዝግንኙነት ስራዎቹን ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር ተቋማት ተሞክሮዎች በማጋራቱን ለዘርፉ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆኑ ተገለፀ

ባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን የህዝግንኙነት ስራዎቹን ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር ተቋማት ተሞክሮዎች በማጋራቱን ለዘርፉ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆኑ ተገለፀ

            ህዳር 26/2018 ዓ.ም
           **አዲሰ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ከሰተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድሀኒት አስተዳደር ባለስልጣን፣ለትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፣ ለአዲስ አበባ የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን  እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬቶች የኮሙኒኬሽንና የህዝግንኙነት ስራዎቹን ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋራ ።

በልምድ ልውውጡ  የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ  የደንብ ማስከበር  ባለስልጣን  የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት  በዳይሬክቶሬት ከተዋቀረ አጭር አመታት ቢሆንም ከባለስልጣኑ አመራሮች ጋር በመግባባት መስራት በመቻሉ የተሻለ የሚዲያ ግንኙነትና  የገፅታ ግንባታ ስራዎች መሰራት መቻሉ  ገልፀዋል።

በልምድ ልውውጡ ለሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራዋች በአመራሩና በባለሙያው በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት  የድምፅና የምስል ስቱዲዮ በማስገንባት  የደንብ መተላለፎችን ግንዛቤ በመፍጠር እንዲቀነሱ በሜንስትሪሚንግና በሶሻል ሚዲያዎች እየተሰራ መሆኑን ተገልፀዋል።

ልምድና ተሞክሮ ለመውሰድ የመጡት ዳይሬክቶሬቶች ከተቋቋመበት በአጭር ጊዜ የስራዎቹ ቁርጠኛ በመሆን  ስቱዲዮዋች  በማስገንባት የተሻለ ስራዎች በመስራቱ ተቋሙን መርጠው መምጣታቸው ገልፀው ለሌሎች ተቋማት የተሞክሮ መቅሰሚያ ማዕከል እንዲሆን ለሰሩ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች አመስግነዋል።

በልምድ ልውውጡ የስቱዲዮ ግንባታው ሂደት፣ የተለያዩ ሚዲያዎችን  በማሳተፍ የተሰሩ ስራዎችን፣የሶሻል ሚዲያ ተከታይን አጠቃቀም ፣ የህትመት ውጤቶችን ዝግጅት፣ የህዝብ ግንኙነት ስራዎች፣ የግባቶች አጠቃቀም እና የሬዲዮና ቴለቪዥን  ስራዎች በተመለከተ ያለውን ተሞክሮ አጋርቷል።

ለልምድ ልውውጥ የመጡት ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎች ለተደረገላቸ መልካም አቀባበል  አመስግነው ልምድ ልውውጡ ተጠናቋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments