ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ አካሄደ::
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ አካሄደ::
ኅዳር 29/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰኞ ማለዳ አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት ልምድና ዕውቀት ሽግግር የሚካሄድበት የወረቃማ ሰኞ የአብሮነት መደረክ በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂድዋል።
በመድረኩ "የመደመር መንግስት እይታ; የዘርፎች እምርታ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ በእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮ/ል አድማሱ ተክሌ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ የወረደ የመንግስት ስራ ሰዓት ማክበር የተመለከተ መመሪያ ሰነድ በባለስልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂድዋል።
በውይይቱም እንደነዚህ ያሉ መድረኮች መዘጋጀታቸው ሰራተኞችን ከማንቃትና አጽኖት ከመስጠት ባሻገር መብትና ግዴታቸውን በማሳወቅና በማዋሀድ የአገልሎት አሰጣጡ የተሳለጠ እንዲሆን ያደርጋል ፣ እንደ ተቋም የወረዱ መመሪያዎች ወደ ዘርፍና ዳይሬክተር በማቅረብ እንደ ግለሰብ ወደተግባር የመግባቱ ሁኔታ ላይ ሊሰራበት ይገባል በሚሉና ሌሎች ሀሳቦች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments