ባለስልጣኑ "ህገወጥ እርድና እንስሳት ዝዉዉርን...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ "ህገወጥ እርድና እንስሳት ዝዉዉርን በህብረተሰብ ተሳትፎ እንቀንሳለን!" በሚል መሪ ቃል በከተማ ያስጀመረውን የህብረተሰብ ውይይት በሁሉም ወረዳዎች እየተካሄደ ነው ‎

ባለስልጣኑ "ህገወጥ እርድና እንስሳት ዝዉዉርን በህብረተሰብ ተሳትፎ እንቀንሳለን!" በሚል መሪ ቃል በከተማ ያስጀመረውን የህብረተሰብ ውይይት በሁሉም ወረዳዎች እየተካሄደ ነው

                 ‎ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
‎                **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ‎በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤቱ አስተባባሪነት በደንብ ቁጥር 150/2015 ህገወጥ እርድና የእንስሳት ዝዉዉርን በሚመለከት ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት ንቅናቄ መድረክ አካሄደ ።

በመድረኩም የሀይማኖት አባቶች፣ የሆቴል ባለቤቶች፣ የማህበረሰብ ተወካዮች የጽዳት ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የሀይማኖት አባቶች መርሃ ግብሩን በፀሎት አስጀምረዋል።

‎የዉይይቱን የመነሻ ሰነድ የጽህፈት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር ደሳለኝ ሌንጮ ያቀረቡ ሲሆን ህገወጥ እርድ የከተማዋን እድገትና ውበት በመቀነስ  ለሀገር ኢኮኖሚ እና ለማህበረሰቡ ጤና ጠንቅ መሆኑን አስረድተዋል።

‎ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ሰፊ ዉይይት ያደረጉ ሲሆን በዉይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች መድረኩን የመሩት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር ደሳለኝ እና የወረዳው ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሙላት ንጉሴ፣ የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም መኮነን ህገወጥ እርድ በማህበረሰቡ እና በሀገር የሚያሳድረዉን ተጽዕኖ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመድረኩ ‎ህገወጥ እርድን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ድርሻ መሆኑን የተገለፀ  ሲሆን  የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments