ባለስልጣኑ በተለያዩ ጊዜ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተወረሱ 22750 የሺሻ መጠቀሚያ እቃዎች እና 5000 ግራም አደንዛዥ ዕፅ ተወገዱ
ባለስልጣኑ በተለያዩ ጊዜ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተወረሱ 22750 የሺሻ መጠቀሚያ እቃዎች እና 5000 ግራም አደንዛዥ ዕፅ ተወገዱ
ህዳር 04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፅ/ቤቱ በተለያየ ጊዜ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተወረሱ 22,750 የሺሻ መጠቀሚያ እቃዎች እና 5000 ግራም አደንዛዥ ዕፅ መወገዳቸውን ተገለፀ።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ ከህብረተሠቡ የሚመጡ የተለያዩ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ለወንጀል መንስኤ በሆኑ ቦታዎች ላይ የኦፕሬሽን ስራዎችን በማከናወን አደንዛዥ እፅ ከህገወጦች በመያዝ እንዲወገድ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
በከተማዋ የሚስተዋለውን ህገ ወጥነት እና ወንጀልን ለመከላከል በክፍለ ከተማው ሺሻ በሚያስጨሱ ህገወጦች ላይ በተለያየ ጊዜ በተከናወነ የኦፕሬሽን ስራ የሺሻ እቃዎችን መያዝ እንደተቻለ እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እቃዎቹ እንዲወገዱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በሺሻ እቃ ማስወገጃ ቦታው ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትና ሌሎች የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።
በእለቱ አዋኪ ድርጊቶች የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ በማሳጣት የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ወላጆችና ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸው ሊወጡ እንደሚገባ ተመላክቷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments