አለም አቀፍ የህፃናት እና የነጭ ሪቫን ቀንን...

image description
- In code inforcement    0

አለም አቀፍ የህፃናት እና የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ የባለስልጣኑ የማዕከል ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

አለም አቀፍ የህፃናት እና  የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ የባለስልጣኑ የማዕከል ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

           ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም
             **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አለም አቀፍ የህፃናት እና  የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ ለባለስልጣኑ የማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በመድረኩ የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ  አበባ እሸቴ   በሴቶችና ህፃናት ላይ ፆታን መሰረት ያደረጉ ማንኛውም ጥቃት  ተቀባይነት የሌላቸው በመሆኑ ጥቃቱን ለማስቆም ሁሉም ሰው በትብብር እና በቅንጅት መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።

አያይዘውም ህፃናት መብታቸው ተከብሮላቸው በአዕምሮ በልፅገው እንዲያድጉ በከተማ ደረጃ የህፃናት መጫዎቻ ቦታዎች ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰሩ መሆኑን ተናገረዋል፡፡

በመድረኩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ቢሮ በመጡት ወ/ሮ  ራሄል  ሙሉጌታ አማካኝነት የነጭ ሪቫንና የህፃናት ቀንን አስመልክቶ ሰነድ በማቅረብ ለተሳታፊዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

በስልጠናው  ስለ ፃታዊ ጥቃት ምንነት ፣  ስለ ፃታዊ ጥቃት መገለጫዎች፣ ስለ ኢኮኖሚያዊ ጥቃት፣ አካላዊ ጥቃት፣  ወሲባዊ ጥቃትና ጥቃቶች ስለሚያስከትሉት የስነልቦና ጫና በዝርዝር አስረድተዋል።

የዘንድሮ የነጭ ሪቫንና ቀን ”ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ’’  በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ እንዲሁም  የህፃናት ቀን  “የህጻናት ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁሉም  ሕጻናት’’  በሚል መሪ ቃል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ34ኛ በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ እንደተከበረው በመግለፅ  ቀኑን  በስልጠና ታሳቢ መደረጉ  አስፈላጊ መሆኑ አሰልጣኟ ገልፀዋል፡፡

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments