ባለስልጣኑ የቅሬታና አቤቱታ ማስተዳደሪያ ድረ-ገፅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::
ባለስልጣኑ የቅሬታና አቤቱታ ማስተዳደሪያ ድረ-ገፅ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::
ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቅሬታ አስተዳደር (complaints Management) ድረ-ገፅ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለማዕከልና ክ/ከተማ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በተጋበዙ አሰልጣኞች በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሰጥቷል።
በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የባለስልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ስልጠናው የቅሬታና አቤቱታ አፈታት ስርዓትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የምላሽ ስርአቱን በማሳለጥ ግልፅና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ሆኖ በለማው ድረ-ገፅ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን በመግለጽ ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል በስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመቀጠል የባለስልጣኑ የቅሬታ አስተዳደር (complaints Management) የውስጥ ሰራተኛ ቅሬታ ማቅረቢያ ድረ-ገጽ በሚመለከት በባለስልጣኑ የውስጥ ሰራተኛ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባል ወ/ት ብሌን አለማየሁ እና ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የICT ባለሙያ ወ/ሮ መቅደስ ፍታ ስለ ሰራተኞች የቅሬታ አቀራረብና አፈታት በድረ-ገጹ አጠቃቀም ዙሪያ ሰነድ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሶፍት ዌር ኢንጂነር ባለሙያ አማኑኤል መኮንን በባለጉዳይ ቅሬታ፣ አቤቱታና ጥቆማ ማቅረቢያ ድረ-ገጹ አጠቃቀም ፣ የቅሬታ፣ አቤቱታና ጥቆማ አቀራረብ፣ አፈታትና ምላሽ አሰጣጥ ሂደት የሚያሳይ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በቀረበው የቅሬታ አቤቱታ ማስተዳደሪያ ድረ-ገጽ ላይ ከሰልጣኞች የተነሱ ሀሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች ላይ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ የቅሬታና አቤቱታ አፈታት ዳይሬክተር ወ/ሮ ነፃነት እና የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የሶፍት ዌር ኢንጂነር ባለሙያው አቶ አማኑኤል ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments