ባለስልጣኑ በአደይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ማጠቃለያ ውይይት መድረክ አካሄደ
ባለስልጣኑ በአደይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ማጠቃለያ ውይይት መድረክ አካሄደ
09/04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በወቅታዊ የተቋቋሙ ጥንካሬዎች እና አንዳንድ የአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ ከማዕከል አስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች በተገኙበት ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የውይይት መድረክ በአድዋ ሙዚየም መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።
ውይይቱን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ባስመዘገበው ውጤት ልክ ወደፊት የሚጠበቁበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በአቅም ግንባታ ስልጠናው እራሱን በማደስ ከተማዋ በምትፈልገው ፍጥነት የማይጓዝ እና የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት በማይችል አመራርና ኦፊሰር እንደማይታገስ አሳስበዋል ።
ማንኛውንም የደንብ መተላለፍ ተግባራት በሚፈጸም ወቅት ዝቅ ብሎ በቀናነት ህብረተሰቡን ለማገልገል ፍቃደኛ በማይሆን አካላትና በብልሹ አሰራር ተግባር ላይ ተሳትፎ የተገኘ አመራርና ኦፊሰሮችን ተጠያቂ የሚያደርግ እርምጃ እየወሰደ ዉጤታማነቱን አጠናክሮ በማስቀጠል ተልዕኮውን እውን እንደሚያረግ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።
የተሰጠን ተልዕኮ ከመፈጸም አንጻር ሽፍት አስተባባሪዎች ፣ ሽፍት መሪዎች እና ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በጥንካሬና በድክመት እንዲሁም የሚስተዋሉ የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመገምገም የተዘጋጀ ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል ።
በሰነዱ ተቋሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ ውጤታማ የሆነባቸውን ተግባራቶች ሰውተኮር ስራዎች እንዲሁም በእቅዱ ልክ ያልፈጸማቸው ጉዳዮችና በአንዳንድ አመራርና ኦፊሰሮች የሚፈጸሙ የስነምግባር ጉድለቶች ተመላክተዋል።
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን መዋቅር ተቋሙ በአዋጅ ፣ በደንብና መመሪያ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በአግባቡ እንዳይወጣ የሚያደርጉትን ችግሮች በመለየት በመፍትሔ ላይ መግባባት እንዲቻል ዓላማ ያደረገ መድረክ መሆኑን አቶ እዬብ ገልጸዋል
በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የተሰጠው ስልጠና ተቋሙን ከፍ ያለ ደረጃ ለማድረስ ከህብረተሰቡ ጋር ምክክር በማካሄድ በታዩ ውስንነቶች እና የስነምግባር ጉድለቶችን ለማስተካከል የተካሄደና በዛው ልክ አቅም የተገነባበት እንደነበር ገልጸዋል ።
አክለውም በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን በሚገባ በማስተካከል ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ስነምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ገልጸዋል ።
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዳይቱ ካምፖስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አስተባባሪዎች የእውቅና ሽልማት ተካሂዷል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments