ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመከላከል በህብረተሰቡ ሚና ላይ ግንዛቤ ሰጠ።
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመከላከል በህብረተሰቡ ሚና ላይ ግንዛቤ ሰጠ።
10/04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ደንብ መተላለፍና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመከላከል የህብረተሰቡን ሚና ለማሳደግ ለባለድርሻና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በባለስልጣኑ አዳራሽ ሰጥቷል።
በመድረኩ መጀመሪያ አዋጅ 84/2016 ላይ መሰረት ያደረገ የተቋሙን ተግባርና ኃለፊነት ለማስገንዘብ የተዘጋጀ ሰነድ በባለስልጣኑ የህግ ክፍል ቡድን መሪ አቶ ብርሀኑ ኮርሳ እንዲሁም ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከላከል ሂደት ላይ በሚያጋጥሙ የስነ-ምግባር ግድፈቶችና የመልካም አስተዳደር ክፍተቶች ዙሪያ በባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ሰፊ ሰነድ ቀርቧል።
ከቀረቡት ሰነዶች በመነሳት ተቋሙ በተሰጡት አዋጅና ደንብ መሰረት እየተወጣቸው ስለሚገኙ ተግባርና ኃለፊነት ፣ የደንብ መተላለፍን ለመከላከል እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ፣ የመልካም አስተዳደርና የስነ-ምግባር ግድፈቶች ዙሪያ ሊወሰድ ስለሚገባ ጥንቃቄ፤ የመከላከያ መንገድ እና መሰል ነጥቦች ላይ ሀሳብና አስተያየቶች በማንሳት ሰፊ ውይይት ማካሄድ ተችሏል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ከቀረቡት ሰነዶች በመነሳት በአካባቢያቸው ግንዛቤ የመስጠት ስራውን በማስቀጠል የደንብ መተላለፍና መልካም አስተዳደር ተግዳሮቶችን የመከላከልና የማስቆም ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በማሳሰብ መድረኩን አጠናቀዋል።
ዘገባው ፡-የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments