በማዕከል የተጀመረው የአደይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ...

image description
- In code inforcement    0

በማዕከል የተጀመረው የአደይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ስልጠና የማጠቃለያ ግምገማዊ የውይይት መድረክ በዛሬው እለትም በክፍለ ከተማ ደረጃ ተካሂዷል 11/04/2018 ዓ

በማዕከል የተጀመረው የአደይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ስልጠና የማጠቃለያ ግምገማዊ የውይይት መድረክ በዛሬው እለትም በክፍለ ከተማ ደረጃ ተካሂዷል

         11/04/2018 ዓ.ም
         **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በወቅታዊ የተቋቋሙ ጥንካሬዎች እና የአሰራር ክፍተቶች በተመለከ  በማዕከል የተጀመረው የአደይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ስልጠና የማጠቃለያ ግምገማዊ የውይይት መድረክ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ በዛሬው እለትም በክፍለ ከተማ ደረጃ ተካዷል።

ውይይቱን በትላንትናው እለት በአራት ክላስተር የተካሄደ ሲሆን  በዛሬው እለትም ተቋሙ ባስመዘገበው ውጤት ልክ ወደፊት የሚጠበቁበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ተቋሙ በአቅም ግንባታ ስልጠና በማዘጋጀት ስልጠናውን በተግባር በማዋል ከተማዋ በምትፈልገው ፍጥነት አገልግሎት መስጠት በሚቻልባቸው የአሰራራ ግልፅነትና ተጠያቂነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

በመድረኮቹ በብልሹ አሰራር ተግባር ላይ ተሳትፎ የተገኘ አመራርና ኦፊሰሮችን ተጠያቂ የሚያደርግ እና አስተማሪ እርምጃ  እንደሚወሰድ ተገልጿል ።

በግምገማዊ የውይይት መድረኩ በአንዳንድ አመራርና ኦፊሰሮች የሚፈጸሙ የስነምግባር ጉድለቶችና ችግሮች በመለየት ወደ ግለሰብ በማውረድና በመወያየት  መግባባት ላይ በመድረስ በቀጣይ እንዲስተካከሉ እና ተጨባጭ መረጃ የተገኘባቸው አካላትም በመመሪያው መሰረት አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በዕለቱ ሰልጣኞች የተለያዩ ሃሳቦች እና አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን በተነሱት ሃሳቦች ላይ በማዕከል እና በክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።


መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments