ባለስልጣኑ ከክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ የስራ የአፈጻጸም ጥንካሬዎች እና በአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ ውይይት አደረገ
ባለስልጣኑ ከክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ የስራ የአፈጻጸም ጥንካሬዎች እና በአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ ውይይት አደረገ
13/04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የማኔጅመንት አመራሮች በክ/ከተማ ደረጃ ከአዳይቱ ፖሊስ ማሰልጠኛ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ ሽፍት አስተባባሪዎች ፣ሽፍት መሪዎችና ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የተደረገው የማጠቃለያ ግምገማዊ ውይይት ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ ።
በውይይቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን
በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፍ ተያይዥ ህገወጥ ተግባራት የመከላከል እና እርምጃ የመውሰድ ተግባር ሲከናወን ስነ ምግባር በመላበስና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በውይይት መድረኩ የአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበሰር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ከአደይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ስልጠና ካጠናቀቁ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የተደረገውን የማጠቃለያ ግምገማዊ የውይይት በተመለከተ አጭር ሪፖርት አቅርበዋል ።
የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች በሚሰጡት አገልግሎትና በተሰማሩበት የስራ መስክ ሙያዊ ስነ ምግባር በመላበስ እንዲሁም ቅንነት የተሞላበት አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው በመድረኩ ተመላክቷል።
በመጨረሻም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተሰጥቶ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments