ባለስልጣኑ የወንዞችን ብክለት በመከላከል ሂደቱ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የወንዞችን ብክለት በመከላከል ሂደቱ ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሊሆን እንደሚገባ ገለጸ

ባለስልጣኑ የወንዞችን ብክለት በመከላከል ሂደቱ ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ጉልህ ሊሆን እንደሚገባ ገለጸ

               ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
                    **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የአዲስ አበባ ከተማን ወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች  የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂድዋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ማስጀመሪያ ላይ የባለሥልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባስተላለፉት መልእክት የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከተማዋ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ውብ፣ጤናማና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግና ያስቀመጠውን ራዕይ እውን ለማሳካት ከወጡ ደንቦች መካከል የሆነውን ደንብ ቁጥር 180/2017 ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን የማስፈጸም ስራዎችን  የማከናወን ተግባሩን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አያይዘውም የደንቡን ተፈጻሚነት የበለጠ ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ ስለሚኖረው ተግባርና ኃለፊነት ማስገንዘብ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት በማንሳት የተፈጠረውን ግንዛቤ በባለቤትነት በመገንዘብ ወንዞችን ከብክለት የመከላከል ተግባሩ የበለጠ ማስቀጠልና የአምባሳደርነት ሚናቸውንም ሊወጡ እንደሚገባ በማስገንዘብ መድረኩን አስጀምረዋል።

በመቀጠል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በመጡ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሙላቱ ወሰኑ የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞችን ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ላይ አትኩሮቱን ያደረገ ሰነድ አቅርበዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ በመነሳት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቶቹ ስልጣንና ተግባር በሚመለከት ፣ ወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል መወሰድ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ፣ ደንቡን ተላልፈው ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ አካላት (ግለሰቦች፣ ተቋማትና ድርጅቶች) ላይ እየተጣሉ ስላሉ የቅጣት ሰንጠረዦች እንዲሁም በቀጣይ በጋራ መሰራት ባለባቸው ተግባራት ላይ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተዋል።

ከተነሱት አስተያየቶች በመነሳት የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን እና የቁጥጥር ክትትልና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት መድረኩን አጠቃለዋል።

ዘገባው ፡- የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments