የአምስተኛ ዙር የወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ሰ...

image description
- In code inforcement    0

የአምስተኛ ዙር የወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣና ሰልጣኝ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ሰነዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ማሰልጠኛ ገቡ

የአምስተኛ ዙር የወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣና ሰልጣኝ  ፓራ ሚሊተሪ  ኦፊሰሮች ሰነዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ማሰልጠኛ ገቡ

           17/4/2018 ዓ.ም
            ** ሰንዳፋ**     

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የአምስተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር  የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች  ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ  የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመውሰድ ገቡ።

ሰልጣኞቹ ወደ ማሰልጠኛው ሲደርሱ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጠን አማካሪ በወ/ሮ አበባ እሸቴ ጨምሮ በባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪዎች እና በፓሊስ ዩንቨርስቲው ማህበረሰብ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

በስልጠና መክፈቻ መርሀ ግብሩ በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርስቲው ዋና ኢንስፔክተር ዋቅቶላ ታምራት አማካኝነት ቀደም ብለው የሰለጠኑ ሰልጣኞች ሪፓርት ቀርቧል።

ስልጠናው በሀገር ወዳድነት፣ በግጭት አፈታት ፣በመረጃ አያያዝ፣በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ በተግባቦት ክህሎት ፣ የእሳት አደጋን በመከላከል እና የአካል ብቃት ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ተመልክቷል ።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የአቅም ግንባታና የስልጠና ማዕከል መምሪያ  ሃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ዩንቨርስቲው ከባለስልጣኑ ጋር በመተባበር የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ  አማካሪ ወ/ሮ አበባ  አሸቴ  የባለስልጣኑን አመራርና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች አቅም ለማሳደግ የወታደራዊና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና አስፈላጊ በመሆን  ስልጠናውን በአንጋፋው ፖሊስ ዩንቨርስቲ አማካኝነት ማሰጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል።

በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ሥልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት  እንደሚቆይና በመግለፅ ሰልጣኞች ስልጠናው በዲሲፕሊን፣በንቃትና በብቃት እንዲከታተሉ መልዕክት ተላልፏል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments