ባለስልጣኑ የአለም የኤች አይ ቪ ኤደስ ቀን በማስመልከት ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ የአለም የኤች አይ ቪ ኤደስ ቀን በማስመልከት ውይይት አካሄደ
20/04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሜንስትርሚንግ ቡድን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር " ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት እናረጋግጥ " በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ38ተኛ በሀገራችን ለ37ተኛ ጊዜ የሚከበረውን የአለም የኤች አይ ቪ ኤደስ ቀንን የባለስልጣኑ ኃለፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት ቀኑን ታስቦ ውሏል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ቀኑ በዋነኝነት የሚከበረው በበሽታውን አማካኝነት ሂወታቸውን ላጡ አካላት መታሰቢያና በቀጣይ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል ።
የዓለም ኤች አይቪ ኤድስ ቀንን በተመለከተ የውይይት ሰነድ ከአዲስአበባ ጤና ቢሮ የኤች አይቪ ሜንስትርሚንግ ቡድን መሪ በአቶ ወንድሙ ደንቦ ቀርቧል።
ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ዛሬም ስርጭቱ እየሰፋ ገዳይነቱ እየቀጠለ በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ መዘናጋትን በማስወገድ የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሰልጣኙ ገልጸዋል ፡፡
በሽታው በአብዛኛው ሴቶችን እና ወጣቶችን እያጠቃ መሆኑን ያነሱት አሰልጣኙ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ኤች አይ ቪ ኤድስን ከቤተሰቡ እና ከማህበረሰቡ ነጻ ለማድረግ ግንዛቤን የማሳደግ ስራ በባለቤትነት ሊሰራ እንደሚገባ አሰገንዝበዋል።
በሰነዱ የኤችአይቪ ኤድስ አሁናዊ የስርጭቱ ሁኔታ ፣ ስርጭቱ እንዲጨምር ያደረጉ ምክንያቶች ፣ መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ መንገዶች በዝርዝር በአሰልጣኙ ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments