በከተማ አስተዳደሩ የተቋቋመው የሱፐርቪዥን አባላት የባለስልጣኑ የ6 ወራት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ምልከታ አደረጉ
በከተማ አስተዳደሩ የተቋቋመው የሱፐርቪዥን አባላት የባለስልጣኑ የ6 ወራት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ምልከታ አደረጉ
ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበበ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመው የሱፐርቪዥን አባላት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተቋም በመገኘት የ2018 በጀት ዓመት በ6 ወራት በመንግስትና በፓርቲ የተሰሩ የዕቅድ አፈፃፀም ስራዎች ላይ የሰነድና የተግባር ምልከታ አደረገ ፡፡
በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ፅ/ቤት የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ አባይነህ አመርጉ በባለስልጣኑ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተሰራው ስራ ሌሎች ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚገባ መሆኑ ገልፀዋል።
አክለውም ባለስልጣኑ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ላይ በይበልጥ በማተኮር ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ በመስጠት የተሰሩ ስራዎች ለህብረተሰቡ በመግለፅ የተወሰዱ እርምጃዎች ግልፅነት መፍጠሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
በምልከታው የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በ6 ወሩ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ ስራቸው ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ በእውቀት እንዲሰሩ የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠናዎች በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።
አያይዘውም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ለማስተግበር ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ አሰራር ለመፍጠር የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን በመጠቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራዎችን በማጠናቀቅ በቴክኖሎጅ የተደገፉ አሰራር እንደሚዘረጋ ተናግረዋል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments