ባለስልጣኑ የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄደ
ባለስልጣኑ የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄደ
28/04/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የገና በዓልን አስመልክቶ ለማዕከሉ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል ።
በማዕድ ማጋራቱ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ አንድነታችንን በተግባር በማሳየት በዓላቶች በደስታና በጋራ በመሆን ያለንን በማካፈል አብሮነታችን ማጠናከር አለብን በማለት ተናግረዋል፡
አክለውም አብሮነታችንና አንድነታችንን ለማጠናከር ያለንን የማከፈል እሴቶች ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል በማለት በዓሉ የሰላም፣የደስታ እንዲሁም የአንድነት በዓል እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ባለስልጣኑ በነፋስስልክ ላፍቶ፣በቂርቆስና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፅ/ቤቶቹ ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎችና ለሰራተኞቹ ማዕድ ማጋራታቸውና የተለያዩ የበዓል ስጦታዎች ማበርከቱን የፅ/ቤቶቹ ኮሙኒኬሽን ተወካዮች በላኩት መረጃ አመላክተዋል።
በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ የባለስልጣኑ አመራሮች የመልካም በዓል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል በቀጣይ የሰው ተኮር ተግባራቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments