ሰራተኛን በስልጠና በማብቃት ዘመኑ የሚጠይቀውን...

image description
- In code inforcement    0

ሰራተኛን በስልጠና በማብቃት ዘመኑ የሚጠይቀውን አሰራር መከተል እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

ሰራተኛን በስልጠና በማብቃት ዘመኑ የሚጠይቀውን አሰራር መከተል እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
  
                 28/04/2018 ዓ.ም
                   **ሰንዳፋ**   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በአምስተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የአካል ብቃትናና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና  የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሰንዳፋ በሚገኘው በኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲ የማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት ኢትዮጲያ ሀገራችን በበርካታ ዘርፎች በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኖን እና የአለም ትኩረት እየሳባች እንደምትገኝ ገልፀው። ከተማችንንም አዲስ አበባ በተለያዩ ልማቶች በእድገት ላይ ትገኛለች  በተለይም በኮሊደር ልማቱ ስራዎች ላይ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ  ኦፊሰሩ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በባለስልጣኑ ከፍተኛ  እምነት ስላለው የተለያዩ ደንብና መመሪያዎች እንዲያስተገብር ተልዕኮ በመሰጠት ላይ በመሆኑ በእውቀት ላይ ተመስርቶ በቴክኖሎጅ ዘምኖ ጊዜውን የዋጀ አሰራር በመከተል የተጣለበትን አደራ ዝግጁ  መሆን እንዳለበት ዋና ስራ አስኪያጁ አስገንዝበዋል።

ተቋሙ ሰራተኞቹን በስልጠና በማብቃት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በማስተግበር ዘመኑን የሚጠይቀው አሰራር  በመከተል  በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን እንደሚከናወን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከተማዋን እና ሀገርን እያገለገላችሁ በመሆናችሁ አዲስ አበባ ከደረሰችበት ነባራዊ ሁኔታ እና እስማርት ሲቲ ከማድረግ አኳያ በእኩል እስታንዳርድ ለመጓዝ እንዲሁም ከተማዋን የሚመጥኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ሆናችሁ እንድትወጡ በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ምክትል ስራ አስኪያጁ አክለው እንደተናገሩት ሰው ክቡር ነው ብሎ በሰብዓዊነት የሚያይ ኦፊሰር ለመፍጠር በዚህ የስልጠና ሂደት የሰብዓዊ መብት  አያያዝ ስልጠና ተሰቷል። በዚህም ይህንን እና ሌሎች ስልጠናዎችን ከግንዛቤ በማስገባት  በቀጣይ በስራ አለም ላይ ልታውሉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ዋና ስራ አስኪያጁ ለሰልጣኞች የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ የአሰራር ክፍተቶችን በመቀልበስ እና በታነፀ ማንነት እንዲሁም ህብረተሰቡን በቅን በአገልጋይነት ስሜት እንዲያገለግሉ አሳስበው ስልጠናውን ላጠናቀቁ የአምስተኛ ዙር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments