ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር የስድስት ወ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

          01 / 05  / 2018 ዓ.ም
           አዲስ አበባ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት  የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸሙን የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተገመገመ ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከባለስልጣኑ ጋር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባከናወናቸው ውጤታማ ስራዎች በከተማዋ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ማስፈን እና በከተማው የሚታዪ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል። 

አክለውም የአገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር፣ ስነምግባር በመላበስና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ስራዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ህብረተሰቡ በቀናነት ማገልገል እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት  ውጤታማ የሆኑ አፈፃፀሞች የተገኙት ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋቱ ስራዎችን በዕቅድ መሠረት ማከናወን በመቻሉ ስለሆነ ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የቀጣይ ሰራዎች ላይ በእቅድ መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

በ7/24 የስራ ባህል በመስራት በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስና ሰላምና ጸጥታ የተጠበቀ እንዲሆን ለነዋሪዎችና ለእንግዶች ከተማችን ምቹ እንድትሆን በርካታ ተግባራት መከናወኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ እስከአሁን ባለው ከ206 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማስገባት መቻሉን እና በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 87.6% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮን የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።

ህዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ የሚያስችሉ የሰላም ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አደረጃጀቶችን በአደረጃጀትና በግብዓት ማጠንከርና የጸጥታ አጋዥ ሃይል እንዲሆኑ ማስቻል አንደሚገባ ተገልጿል ።

ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ ሰላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን አስቀድሞ በመለየት እና የተፈጸሙ ድርጊቶችን ሳይባባሱ በቅንጅት በመከላከል የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ላይ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል።

በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ውይይት በማካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በግማሽ ዓመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር ክፍተቶችን በማረም ለተሻለ ውጤት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments