የስራ አፈጻጸምን መገምገም ለቀጣይ ስኬት መሰረት ነው" ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
"የስራ አፈጻጸምን መገምገም ለቀጣይ ስኬት መሰረት ነው" ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
ጥር 5/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ 6 ወር አፈጻጸሙን የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የ11 ክፍለ ከተማ እና የ119 ወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰበሰቢያ አዳራሽ ገምግሟል።
የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በንግግራቸው ተቋሙ በ2017 ዓ.ም ከፍተኛ ስኬትን ማስመዝገብ መቻሉንና ከስኬቱ በመነሳትም የ2018 እቅድ በማዘጋጀትና በማውረድ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች ፣ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የማዘጋጀት እንዲሁም ተቋምን በቴክኖሎጂ የመገንባት ስራዎችን በማከናወን በ6 ወሩ የደንብ መተላለፎች በ87 % መቀነስ መቻሉ ገልጸዋል።
የስራ አፈጻጸምን መገምገም ለቀጣይ ስኬት መሰረት ነው ያሉት ኃላፊው መድረኮች መዘጋጀታቸው በጥንካሬ የሚጠቀሱተን የበለጠ ለማሻሻልና በክፍተት የታዩትንም በመለየት ትኩረት ሰጥቶ ለመስራትና በስኬት ለመወጣት ትልቅ ግብአት እንደሚሆን በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑን በመግለጽ መድረኩን አስጀምረዋል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የመጀመሪያ 6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮ/ል አድማሱ ተክሌ እንዲሁም ከ11 ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች ውስጥ የተመረጡ 4 ክፍለ ከተሞች የ6ወር እቅድ አፈፃፀም ላይ ፈጻሚን ከማብቃት አንጻር የተሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ከማዘመንና የደንብ መተላለፎች ከመቀነስ አኳያ የታዩ ጥንካሬዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲሁም የታዩ ምርጥ ተሞክሮዎች በሚመለከት በሪፖርቶቹ በማካተት አቅርበዋል።
በመድረኩ ከተሳታፊዎች ተቋሙን ማዘመንና smart office ከማድረግ ፣ ከመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል እንዲሁም የወረቀት ስራን ከመቀነስና ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ ከመተካት አንጻር የተሰሩ ተግባራት መካተታቸውና የአሰራር ሂደቱን ማሳየቱና ተሞክሮዎችን እርስ በርስ ለመጋራት መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው የሚሉና መሰል ነጥቦችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ስ/አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በግምገማው የተነሱ ሀሳቦችን በእኔት ስሜት በመረዳትና በመውሰድ ወደ ተግባር መቀየር በቀጣይ የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸው የቀጣይ ስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማዊ መድረኩን አጠቃለዋል ።
መረጃው ፡- የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments