ባለስልጣኑ በስድስት ወራት ከደንብ ተላለፊዎችና ከተወረሱ ንብረቶች ሽያጭ ከ206 ሚሊዮን ብር በላይ ለከተማው ልማት እንዲውል ወደ ፋይናንስ ገቢ መደረጉ ተገለፀ
ባለስልጣኑ በስድስት ወራት ከደንብ ተላለፊዎችና ከተወረሱ ንብረቶች ሽያጭ ከ206 ሚሊዮን ብር በላይ ለከተማው ልማት እንዲውል ወደ ፋይናንስ ገቢ መደረጉ ተገለፀ
6/05/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም የተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከማዕከል ዳይሬክተሮች ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂደ ።
የባለስልጣኑን የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በግማሽ አመት ሪፖርቱ በአገልግሎት አሰጠጥ፣በመልክም አስተዳደር ፣በሰው ተኮር ተግባራት ፣ በግንዛቤ ፈጠራ ፣ በቅንጅታዊ አሰራር እና በከተማዋ የሚስተዋሉ የተለያዩ ደንብ መተላለፎችን የመከላከል የመቆጣጠር እርምት ለሚያስፈልጋቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድ አንፃር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በሪፖርቱ በከተማ አስተዳደሩ ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ በስድስት ወሩ ከ206 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ከተማው ፋይናንስ ለከተማው ልማት ስራዎች ገቢ መደረግ መቻሉም በሪፓርቱ ተገልጿል።
በውይይቱ ብልሹ አሰራርን ከመታገል አንፃር፣ህገወጥ ተግባራትን ሙሉ በሙሉ ከማጥፋት አንፃር ፣ በግዥና ንብረት አጠቃቀም ዙርያና የተለያዩ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች በቀረበው የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ዙሪያ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችና ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments