ባለስልጣኑ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሰራውን የአቅ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሰራውን የአቅመ ደካማ ቤት አጠናቆ ለባለቤቶቹ አስረከበ

ባለስልጣኑ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሰራውን የአቅመ ደካማ ቤት አጠናቆ ለባለቤቶቹ አስረከበ

               08/05/2018 ዓ.ም
               **አዲስአበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቂርቆስ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ወረዳዎችን በማስተባበር በክፍለ ከተማው ወረዳ 02 ለሚገኙ አቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክቧል ።

በምርቃት መርሐ ግብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሰው ተኮር ተግባራቶች ላይ ሰፊ ስራ እየሰራ እንዳለ በመግለፅ በቀጣይ ባለስልጣኑ ሌሎች ክፍለ ከተሞችም በማስተባበር ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

በመድረኩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ እንዳሉት ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ከሚሰራቸው ዘጠኙም ህገወጥ የደንብ መተላለፍ መከላከልና መቆጣጠር በተጨማሪ ሰው ተኮር ስራዎች እና አቅመ ደካሞችንም የስራው አንዱ አካል አድርጎ እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀው ለዚህም 580,000 ብር  በማውጣት የወ/ሮ ጀማነሽ መታደሱን ገልፀዋል ።

አክለውም ቤቱ ከዚህ በፊት ለአቅመ ደካማ በማይመች ሁኔታ የሚኖሩበት ሲሆን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ በመነጋገር የፈራረሰውን
ቤት በማፍረስ መልሶ አስገንብቶ በሚያምር መልኩ ለባለቤቶቹ ማስረካበቸውን ገልጸዋል ።

ቤቱ የተገነባላቸው ወ/ሮ ጀማነሽ ከዚህ በፊት ይኖሩበት የነበረውን ህይወት አስቸጋሪ እንደነበር መመግለፅ  ለተደረገላቸው ነገር ሁሉ ለደንብ ማስከበር ላቅ ያለ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ደንብ ማስከበር የመደበኛ ስራው በውጤት ከመፈጸም ባሻገር እየሰራ የሚገኘው የሰው ተኮር የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት እጅግ የሚበረታታ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኃላፊ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ  ጠንክረን ከሰራን መቀየር መለወጥ የማንችለው ነገር የለም ሰርተን  በተግባር ቤቱን ለባለቤቶቻቸው አስረክበናል በማለት  ይህ ዓይነት በጎ ተግባርን ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ለቀጣይ ሰርቶ የሚያስረክበውን 2ተኛ የሚታደስ ቤት በዛሬው ዕለት በቂርቆስ ክ/ከተማ አስጀምረዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments