ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታና በሰብ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታና በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ላይ ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታና በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ላይ ስልጠና ሰጠ

                08/05/2018 ዓ.ም
                   **ሰንዳፋ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለስድስተኛ ዙር ነባር ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ኦፊሰሩን ለተልዕኮ ብቁ ለማድረግ የተዘጋጀ ስልጠና የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮችና የስልጠናው አስተባባሪዎች በተገኙበት በሰንዳፋ የዩኒቨርሲቲው አዳራሽ ግምገማዊ ስልጠና ሰጥቷል።

የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና የቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደ መስቀል የትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ስራ ላይ ኦፊሰሩን ለተልእኮ ብቁ ከማድረግ አንጻር ሊሰሩ ስለሚገባቸው ስራዎች እንዲሁም የኦፊሰሩን ኃላፊነት ለማስገንዘብ ታልሞ የተዘጋጀ ግምገማዊ ስልጠና መሆኑን ገልጸው ተቋሙ ከስነ-ምግባር አኳያ የሚገኝበት ደረጃና ነባራዊ ሁኔታ ፣ የደንብ መተላለፍ መንስኤና ተፅዕኖ ፣ ተግዳሮትና የመፍትሄ ኃሳብ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል።

በመቀጠልም ከተሳታፊዎች ተቋምን እንደ ተቋም ለመገንባት ተልእኮን ከአመራር ተቀብሎ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ፣ ከሚታዩ የስነ-ምግባር ጉድለቶች ፣ ከህግ ተፈጻሚነት ጋር በተያያዘ ፣ ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ አንጻር ስላሉ ክፍተቶች ፣ ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ እና በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰር ከመፍጠር አኳያ ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ ሰፊ ውይይት ተካሂድዋል።

በመጨረሻም በተነሱ ጥያቄና ሀሳቦች ዙሪያ በባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እና የስልጠና አስተባባሪዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ የትውልድ ስነ-ምግባር መገንባት ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመዋጋትና ሰብአዊ መብትን ከማስጠበቅ አንጻር ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ እና በተባበረ ክንድ የተቋሙን ራዕይ ሊያሳካ እንደሚገባ በማሳሰብ ግምገማዊ ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments